• hace 7 años
Avocado Face Mask - Amharic - አቮካዶ የፊት ጭንብል - በቤት ውስጥ የሚሰሩ የአቮካዶ የፊት መዋቢያዎች- እንዴት እንደሚሰሩ\r
የአቮካዶ የፊት መዋቢያዎችለቆዳዎ አስደናቂ የውበት ምንጭ ናቸው፡፡ ፍራፍሬው ብዙ ማዕድናትን እንደ ብረት፣ ፖታሲየም፣ ካልሺየም፣ ሶዲየም፣ መዳብ፣ ማግኔዢየም ወ.ዘ.ተ የያዙ ናቸው፡፡ ቪታሚን ኤ፣ ኢ፣ ቢ እና ኬንም የያዙ ናቸው፡፡ የዚህ የተለየ ውህድ ውጤት የአቮካዶ የፊት መዋቢያ የላይኛውን ቆዳ በመዝለቅ የታችኛው ክፍል የሚደርስ ሲሆን በደረቅ ቆዳ ላይ የመለጠጥ ባህሪን ይሰጣል፡፡ \r
በቤት ውስጥ የሚሰራው የአቮካዶ የፊት መዋቢያ ከተፈጥሮ የፊት መዋቢያዎች መካከል በጣም ምርጡ ሲሆን ቆዳን በመመገብ እና ጥንካሬን በመስጠት ይታወቃል፡፡ ይህ ፍራፍሬ ለቆዳ ተስማሚ በሆኑት ማዕድናት እንደ ብረት፣ ካልሺየም፣ ፖታሲየም፣ ሶዲየም፣ መዳብ፣ ማግኔዢየም ወ.ዘ.ተ ቪታሚን ኤ፣ ኢ፣ ቢ እና ኬ እና በፈሳሽ ቅባት የተሞላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ በቤት ውስጥ የሚሰራ የአቮካዶ የፊት መዋቢያ እንዴት እንደሚሰራ ያገኛሉ፡፡\r
የአቮካዶ የፊት መዋቢያ ከኬሚካል እና ከሰው ሰራሽ ግብዓቶች ነፃ ስለሆነ ከብዙ መሸጫ ቦታ ላይ ከሚገዙ የውበት ምርቶች ይልቅ አነስተኛ አለርጂ እና የቆዳ መቆጣት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡\r
አቮካዶን እንደ ግብዓት በመጠቀም የሚሰራው ፊት መዋቢያ በብጉር ለሚጠቃ፣ ለደረቅ እና ቶሎ ለአደጋ ለሚጋለጥ ቆዳ ጥሩ ነው፡፡ \r
የአቮካዶ የፊት መዋቢያ በጣም ደየረቀ ቆዳን የመለጠጥ ሁኔታውን ለማሻሻል የውስጠኛው የቆዳ ክፍሎች ሊደርስ ይችላል፡፡\r
የማርጀት ሂደትን ለመቀነስ አስደናቂ ስራን ይሰራል፡፡\r
አቮካዶ ለጤና ብቻ ሳይሆን ጥሩ የሚሆነው የደረቀ ቆዳንም ያረጥባል፡፡ እንደ እርጎ፣ ወተት እና ማር የያዘው መዋቢያ ለደረቀ ቆዳዎ ጥሩ ነው፡፡ የደረቀ ቆዳዎን ለመመገብ፣ ለማለስለስ፣ ለማንፃት፣ እና ለማርጠብ የራስዎን በቤት ውስጥ የሚሰራ የአቮካዶ የፊት መዋቢያን ይሞክሩ፡፡\r
የአቮካዶ ማር መዋቢያ፡- ይህ ለደረቅ ቆዳ የፊት መዋቢያ ለመስራት ቀላል የሆነው አቮካዶ እና ማር የሚባሉትን 2 የተፈጥሮ ግብአቶችን የሚጠቀም ሲሆን ሁለቱም እንደ የተፈጥሮ ማርጠቢያ ያገለግላሉ፡፡ ይህ መዋቢያ ለቆየ፣ ለተጨማደደ እና ለደረቀ ቆዳ የሚያስገርም ስራ ይሰራል፡፡ አንድ ሙሉ ለሙሉ የበሰለ አዲስ የተቆረጠ አቮካዶ ይውሰዱ፤ ቆዳው እና ዘሩን ያስወግዱ፤ ከዚያም በጎድጓዳ ሳህን ውስጥ የሚበላውን የአቮካዶ የውስጠኛው ክፍል ለንቅጠው ያስቀምጡ፡፡ 1 የሻይ ማንኪያ ማር በመጨመር ተመሳሳይ ውህድ እሰከሚሆን ድረስ ድብልቁን ያማስሉ፡፡ በቆዳው ላይ ያድርጉት እና ለ 10-15 ደቂቃዎች ይተውት፡፡ ለብ ባለ ውሀ ድብልቁን ከፊትዎ ላይ ይጠቡት እና በለስላሳ ፎጣ ፊትዎን በዝግታ ያድርቁ፡፡ \r
የተፈጨ አጃ አቮካዶ የፊት መዋቢያ፡- ይህ እንደ ታላቅ የማርጠቢያ መዋቢያ የሚያገለግል እና የተጎዳ ቆዳን ወደነበረበት ቦታ ለመመለስ ይረዳል፡፡ ½ የበሰለ አቮካዶ እና ½ የተፈጨ አጃ ይውሰዱ፡፡ በተፈጨ አጃ ማሸጊያ ላይ በተፃፈው መመርያ መሰረት የተፈጨ አጃውን ያብስሉት እና ከሚበላው የአቮካዶ የውስጠኛው ክፍል ተመሳሳይ ይዘት ወዳለው ውህድ እስኪመለስ ድረስ ከተለነቀጠው አቮካዶ (ያለ ቆዳው እና ዘር) ጋር ያዋህዱት፡፡ በቆዳዎ ላይ ያድርጉት እና ከ 10-15 ደቂቃ ወይም እስከሚደርቅ ድረስ ይተውት፡፡ ይህን ካደረጉት በኋላ ለብ ባለ ውሀ ይታጠቡት እና በለስላሳ ፎጣ በዝግታ ቆዳዎን ያድርቁ፡፡ \r

Category

📺
TV

Recomendada